Loading
ሆ (፰x) ህዝቡን ፡ ከባርነት ፡ ፈልቅቆ ፡ ያወጣ ከድንጋይ ፡ ላይ ፡ ውኃን ፡ አፍልቆ ፡ ያጠጣ በመሪባ ፡ ውኃ ፡ ያረሰረሳቸው በሲና ፡ ተራራ ፡ ያነጋገራቸው አምላካችን ፡ እርሱ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው እግዚአብሔርን ፡ እንወደዋለን (፬x) ሙዚቃውን ፡ ስትሰሙ ፡ ለቆመው ፡ ለምስጉን ለአምላኬ ፡ ወድቃችሁ ፡ ስገዱ ፡ ሲባሉ እንኳንስ ፡ ሊሰግዱ ፡ ቢንቀለቀል ፡ ቶኑ ፈፁም ፡ ፍንክች ፡ አይሉም ፡ ሶስቱም ፡ ከጨከኑ ከአምላካቸው ፡ ሌላ ፡ ለማንም ፡ አይሰግዱ [1] ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ አናውቅም ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አናመልክም ለአምላካችን ፡ እንሰግድለታለን ለእግዚአብሔር ፡ እንሰዋለታለን አንሰዋም ፡ ለባዳን ፡ አማልክት አንሰግድም ፡ ለሠማይ ፡ ሠራዊት ስግደትን ፡ ስግደት ፡ ለሚገባው ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ገና ፡ ያኔ ፡ ገና ፡ ሠማይ ፡ ምድርን ፡ ሲሰራ (ኡ ፡ ኦ ፡ ኡ ፡ ኦ) ቀላያትን ፡ ሲቀድ ፡ ብርሃንን ፡ ሲያበራ (ኡ ፡ ኦ ፡ ኡ ፡ ኦ) ይሁን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ ለሆነለት ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ለፍጥረታት ፡ አባት ለአምላካችን ፡ ለእርሱ ፡ ለፈጠረን ፡ ጌታ ዘለዓለም ፡ ይድረሰው ፡ ክብርም ፡ ምሥጋና (፪x) ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እናመልከዋለን ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እንሰግድለታለን (፬x) አንሰዋም ፡ ለባዳን ፡ አማልክት አንሰግድም ፡ ለሠማይ ፡ ሠራዊት ስግደትን ፡ ስግደት ፡ ለሚገባው ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እናመልከዋለን ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እንሰግድለታለን (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.