Loading
አዲስ ፡ ልዩ ፡ ነገድ ፡ ተገኝቷል ከአስራ ፡ ሁለቱ ፡ አይደል ፡ ከእስራኤል (፪x) እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ዐይነቱ ፡ የነገዱ ሃያል ፡ ገናና ፡ ነው ፡ ንጉሡ የጸና ፡ መንግሥቱ (፪x) ዜግነት ፡ ቢሉ ፡ ሰማያዊ አለቃው ፡ የሰማይ ፡ የምድር ፡ ፈጣሪ አለ ፡ የሚኖር ፡ ዘለዓለማዊ አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደዚህ ፡ መንግሥት ፡ ሲጋብዘኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ዜግነት ፡ እስኪሰጠኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደዚህ ፡ ግዛት ፡ ሲጋብዘኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ማንነት ፡ እንዲሰጠኝ እኔም ፡ ግዛቱ ፡ ለመግባት ፡ አሰብኩኝ ህገመንግሥቱን ፡ አነበብኩኝ ፡ የተጻፈውን ፡ አንበብኩኝ መግቢያው ፡ መወለድ ፡ ነው ፡ ዳግም የመስቀሉን ፡ ሃይል ፡ አምኖ ፡ መቀበል (፪x) መቀበል ፡ ማመን ፡ በልጁ በመንፈስ ፡ ዳግም ፡ መወለዱ ሌላም ፡ አይደለም ፡ ይሄው ፡ ነው ፡ መንገዱ አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ በማመን ፡ ብቻ ፡ ሲቀበለኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ልጁን ፡ ስቀበል ፡ ተ???በለኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አባቴ ፡ ሆኖ ፡ ልጄ ፡ ሲለኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ለዘለዓለም ፡ ኑሪ ፡ ሲለኝ ጽዮናዊ ፡ ነኝ ፡ በዜግነት ፡ አሁንማ ተረሳስተናል ፡ ከዓለም ፡ ጋራ ፡ ተካክደናል ፡ ከዓለም ፡ ጋራ ሰማያዊ ፡ ነው ፡ ሚናፍቀኝ ፡ የማስበው የምድርን ፡ ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ጽዮንን ፡ ተመኘሁ (፪x) ጨለማው ፡ ጠፍቶ ፡ በርቻለሁ ሰማያዊ ፡ ነው ፡ የምናገረው ስፍራ ፡ ቀይሬ ፡ በቀኙ ፡ ሆኛለሁ አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ በቀኙ ፡ በኩል ፡ አስቀመጠኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ቋንቋዬን ፡ ሁሉ ፡ ቀየረልኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ማንነት ፡ አገኘሁኝ (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደ ፡ መንግሥቱ ፡ ገላገለኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.