Loading
አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፪x) በመከራዬ ፡ ጊዜ ፡ በአፌ ፡ የተናገርኩትን ከአንደበቴም ፡ ያወጣሁትን ፡ ቃሌን ይኸው ፡ እፈጽማለሁ ፡ ለአንተ ፡ ስለቴን (፪x) አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፪x) ጵኑ ግንብ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ ተስፋዬም ፡ ሆነኸኛልና በድንኳንህ ፡ ለዘላለም ፡ እኖራለሁ በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ እጋረዳለሁ (፪x) አቤቱ ፡ አንተ ፡ ስለቴን ፡ ሰምተሃል የልመናዬን ፡ ድምጽ ፡ ከላይ ፡ አድምጠሃል ታዲያ ፡ የሰው ፡ ማዳን ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ ፡ ነው ባገኘኝ ፡ መከራ ፡ ረዳቴ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.