Loading
አለም ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እያረፈ ይኼ ፡ ጌታ ፡ በዚህ ፡ እያለፈ ዝም ፡ አልልም ፡ እጮሀለሁ የዳዊት ፡ ልጅ ፡ እለዋለሁ (፪x) እየሱሴ ፡ የምታልፈው የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x) ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x) የሚጋፋ ፡ ግን ፡ የማይነካ የሚከፋው ፡ ለሰው ፡ ሲሳካ ተው ፡ ቢለኝም ፡ አልተውም ፡ እኔ ጨልሞብኝ ፡ አይለቅ ፡ ዘመኔ (፪x) እየሱሴ ፡ የምታልፈው የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x) ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x) እርሱ ፡ ጠርቶ ፡ ምን ፡ ይለመናል ብር ፡ ወርቅማ ፡ ሰውም ፡ ይሰጣል ልከተልሀ ፡ ፈውስ ፡ አይኔን መብራት ፡ የኔን ፡ ሰውነቴን (፪x) በሰፈሬ ፡ በመንደሬ ሰምቻለሁ ፡ መልካም ፡ ወሬ መታሰሬ ፡ መታወሬ ታሪክ ፡ ይሁን ፡ ያብቃ ፡ ዛሬ አንዴ ፡ ልይህ ፡ አንተን ፡ ዛሬ (፪x) እየሱሴ ፡ የምታልፈው የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x) ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.