Loading
አምላኬ ፡ ፊትህን ፡ መቼ ፡ አየዋለሁ ውዴ ፡ ሆይ ፡ አንተስ ፡ ጋር ፡ መቼ ፡ እደርሳለሁ አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x) እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x) ውኃም ፡ እንጨትም ፡ በሌለበት ነፍሴ ፡ ተጠማች ፡ የአምላኳን ፡ ፊት ሥጋዬም ፡ ናፍቃ ፡ በምድረበዳ ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንድታይ ፡ ወዳ አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x) እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x) ወዳንተ ፡ ወዳንተ ፡ እገሰግሳለሁ (፬x) በመኝታዬ ፡ አስብሀለሁ ማለዳ ፡ ቀትር ፡ አወራሀለሁ ነፍሴ ፡ ከኋላ ፡ ተከተለችህ ውዴ ፡ ወዳጄ ፡ ፍቅሬ ፡ አለችህ አምላክ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ዘወትር ፡ ሲል እምባዬ ፡ በዝቶ ፡ ምግብ ፡ ሲሆነኝ ወደ ፡ ምሥጋና ፡ ማደሪየህ ፡ ልግባ ነፍሴ ፡ እንድትጠግብ ፡ አንተን ፡ አስባ አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x) እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.