Loading
ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x) ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x) መች ፡ እዘገናለሁ ፡ የትላንቱን አስታውሰዋለሁ ፡ እያንዳንዱን (፪x) እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ፡ እኔ ፡ ነኛ ከጐኔ ፡ ሰው ፡ ሳይኖር ፡ ወይ ፡ ጓደኛ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ፡ እኔ ፡ ነኛ የዛሬው ፡ ከፍታ ፡ ታየልኛ (፪x) አዝ፦ አየልኛ ፡ ብዙ ፡ መልካም አየልኛ ፡ ለኔው ፡ ሰላም አየልኛ ፡ ብዙ ፡ እረፍት አየልኛ ፡ የማልፍበት (፪x) ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x) ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x) ያ ፡ ታሪኬ ፡ ዛሬ ፡ ተቀይሮ ሰው ፡ አይቶም ፡ አያውቀኝ ፡ አብሮኝ ፡ ኖሮ ያ ፡ ታሪኬ ፡ ዛሬ ፡ ተቀይሮ የቅርብ ፡ አይለየኝ ፡ አብሮኝ ፡ ኖሮ አትፈልጉ ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ ነኝ በምህረቱ ፡ ብቻ ፡ የቆምኩኝ አትፈልጉ ፡ ሌላ ፡ ራሴ ፡ ነኛ እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ ወደደኛ (፪x) ወደደኛ ፡ ያኔ ፡ ድሮ ወደደኛ ፡ ሌላው ፡ ዞሮ ወደደኛ ፡ ሳይቀየር ወደደኛ ፡ በዛው ፡ ፍቅር (፪x) ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x) ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.