Loading
ሰማያትን ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ እንደማይ ሳየውም ፡ ሩቅ ፡ እንደሆነ አምላኬ ፡ እንደእዛ ፡ አላይህም እግዚአብሔር ፡ እንደእዛ ፡ አላርቅህም ቅርብ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አለህ ፡ አጠገቤ (፬x) ሰማይ ፡ ሰፋህ ፡ አልለው ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ግን ፡ መረጥክ ፡ ልትገባ ፡ ልትቆይ ፡ ከልቤ የታሰበ ፡ ኧረ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ የተዘጋጀ ስለዚህ ፡ አውቃለሁ ፡ አጠገቤ ፡ እንዳለህ አዝ:- ቅርቤ ፡ ነህ ፡ ከጐኔ ፡ ነህ (፪x) ይሰማኛል ፡ ህልውናህ (፪x) የጠየኳቸው ፡ ጥያቄዎች ፡ ሁሉ መልስን ፡ ብትሰጣቸው ፡ ወይም ፡ ቢዘገዩ እነሱንም ፡ አይቼ ፡ ቅርቤ ፡ አላልኩህም እስከ ፡ ፍጻሜ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አመንኩት ፡ ቃልህን አዝ:- ቅርቤ ፡ ነህ ፡ ከጐኔ ፡ ነህ (፪x) ይሰማኛል ፡ ህልውናህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.