Loading
አዝ:- አመሰግናለው (፪x) ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ሕይወትን ፡ ሰጥተኀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞትክና ዋጋዬን ፡ ከፈልክልኝ ፡ አስታረቅከኝ ፡ ከአብ ፡ ጋር በኀጢአት ፡ የጠፋውን ፡ ያጣሁትን ፡ ማንነቴን አገኘሁት ፡ በአንተ ፡ ሆነኅልኝ ፡ መስዋእቴ ሚስጥርህን ፡ ገለጥክልኝ ፡ መጥተህ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ኢየሱሴን ፡ አምኜው ፡ ወስኜ ፡ ስቀበል ከዛ ፡ ቃልህን ፡ ከፍቼ ፡ መረዳት ፡ ስጀምር ለእኔ ፡ ያሰብከው ፡ ሁሉ ፡ ይገለጥልኝ ፡ ጀመር አዝ:- አመሰግናለው (፪x) ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው እንዴት ፡ ብዬ ፡ ዝም ፡ ልበል ፡ አስቸገረኝ ፡ መደበቁ የበራልኝ ፡ እውነት ፡ እኮ ፡ ያስገርማል ፡ ከሌሎቹ እንዴትስ ፡ ይደበቃል ፡ ኧረ ፡ መቼ ፡ ተችሎ ለብዙዎች ፡ ሚስጥር ፡ ሲሆን ፡ ሳየው ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ተገልጦ አዝ:- አመሰግናለው (፪x) ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የበላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ሚመስልህ ገና ፡ እስከዘለዓለም ፡ አንተ ፡ ትመለካለህ አመታት ፡ ተሰጥተውኝ ፡ ብናገር ፡ ብጨምር እንዴት ፡ ብዬ ፡ አውርቼ ፡ ስለአንተ ፡ ልፈጽም አዝ:- አመሰግናለው (፪x) ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.