Loading
ሰው ፡ ሳይል ፡ ቀደስ ፡ በዓይኖቼ ፡ አማትሬ እግዚአብሔር ፡ ያውቃል ፡ የድብቅ ፡ ነገሬን እኔ ፡ ግን ፡ ከቃሉ ፡ አወቅሁ ፡ አንድ ፡ ነገር አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ ጉዳና ፡ አይደል ፡ ኑሮ ፡ ይሁን ፡ ከዚያ ፡ ጀርባ የእልፍኝ ፡ ነገሬን ፡ የሚያይ ፡ አለና እንዲህ ፡ ከሆነ ፡ ኑሮ ፡ ይቅር ፡ ለዘለዓለም አልተጠራሁኝም ፡ ልመስል ፡ ይህን ፡ ዓለም አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ (፪x) አባቴን/ኢየሱስ ፡ እንዲህ ፡ ስል ፡ እለምንሃለሁ ፍለጋን ፡ መሻቴን ፡ ይህን ፡ አድርጌያለሁ (፪x) ከብረህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ነግሠህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪያይ ማነው ፡ እራሱን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚቀድስ ስለ ፡ አምላኩ ፡ ኖሮ ፡ ጌታውን ፡ የሚያስደስት (፪x) እርሱ ፡ ብሩክ ፡ ነዉ ፡ ዘመኑም ፡ የተድላ የድካሙን ፡ ፍሬ ፡ ቁጭ ፡ ብሎ ፡ የሚበላ ሰው ፡ ሳይል ፡ ቀደስ ፡ በዓይኖቼ ፡ አማትሬ እግዚአብሔር ፡ ያውቃል ፡ የድብቅ ፡ ነገሬን እኔ ፡ ግን ፡ ከቃሉ ፡ አወቅሁ ፡ አንድ ፡ ነገር አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ (፪x) ከብረህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ነግሠህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪያይ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.