Loading
አምላካችን ፡ መጠጊያችን ፡ ኃይላችን ባገኘነው ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን (፪x) ሆኖልናል (፪x) የማዳን ፡ ደስታ ፡ ለእኛ ፡ ሰጥቶን በሽታ ፡ መንፈስ ፡ ይኸው ለውጦ ከዚም ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ ለማንም ፡ የለውም ስለወዳጆቹ ፡ የሚሰጥ ፡ እራሱን (፪x) ሄደን ፡ ነበር ፡ ወደ ፡ ተራራ አይተን ፡ ነበር ፡ በብዙ ፡ አቅጣጫ ተስፋ ፡ ሚሆን ፡ ቢታጣም ፡ በዚያ አግኝተናል ፡ የዓይን ፡ ማረፊያ የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ኢየሱስ አምላካችን ፡ መጠጊያችን ፡ ኃይላችን ባገኘነው ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን (፪x) ሆኖልናል (፪x) መች ፡ በቀላሉ ፡ ሚታለፍ ፡ ነበር በሕይወታችን ፡ የሆነው ፡ ነገር እርሱ/ጌታ ፡ ሲመጣልን ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ የተከሰስንበት ፡ እዳችን ፡ ተሻረ (፪x) ሄደን ፡ ነበር ፡ ወደ ፡ ተራራ አይተን ፡ ነበር ፡ በብዙ ፡ አቅጣጫ ተስፋ ፡ ሚሆን ፡ ቢታጣም ፡ በዚያ አግኝተናል ፡ የዓይን ፡ ማረፊያ የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ኢየሱስ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.