Loading
አልቅበዘበዝም ፡ ከዚህ ፡ ወደዚያ ደስታን ፡ ልፈልገው ፡ ከኢየሱስ ፡ ወዲያ ያ ፡ መቅበዝበዜ ፡ ፈጽሞ ፡ ያቆመው ኢየሱስ ፡ ጌታዬን ፡ ያገኘሁት ፡ ቀን ፡ ነው (፪x) በቃ (፫x) ፡ መቅበዝበዜ ፡ አከተመ ፡ እዚያ ፡ ጋር አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (ኢየሱስ ፡ ነው) (፪x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (ኢየሱስ ፡ ነው) (፪x) በጸሎት ፡ ፊቱ?? ፡ ደስ ፡ ላሰኘን በሃዘን ፡ ፈንታ ፡ ደስታን ፡ ከሰጠኝ የምን ፡ ማቀቅር ፡ አንገት ፡ መድፋት ፡ ነው ሃዘን ፡ ለጠላት ፡ ለእኔ ፡ ደስታ ፡ ነው ፈጽሞ ፡ አይከፋኝ ፡ ቤቱ ፡ መጥቼ የሰላሙን/የደስታውን ፡ ምንጭ ፡ እርሱን ፡ አግኝቼ (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (ኢየሱስ ፡ ነው) (፪x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (ኢየሱስ ፡ ነው) (፪x) ጌታን ፡ ላመልከው ፡ ቤቱ ፡ ከመጣሁ አላማ ፡ ብዬ ፡ ጊዜዬን ፡ ከሰዋሁ ማኩረፌ ፡ ይቅር ፡ የልብ ፡ ሃዘኔ እዚህ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ በሃሳብ ፡ መሄዴ ይልቅ ፡ ልደሰት ፡ ላክብረው ፡ ታዲያ ውስጤ ፡ ያለው ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ (፪x) ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፡ ሃሌሉያ (፬x) (ኦ ፡ ሃሌሉያ)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.