Loading
ሸቶናል ፡ የአንተ ፡ መገኘት ፡ ሸቶኛል ሸቶኛል ፡ የአንተ ፡ ህልውና ፡ ሸቶኛል እለመልማለሁ ፡ ብዙ ፡ አፈራለሁ እለመልማለሁ ፡ ብዙ ፡ አፈራለሁ አዝ፦ አልደርቅም ፡ አልደርቅም ፡ ሕያው ፡ ምንጭ አንተ ፡ አለኸኝ ፡ ኢየሱስ (፪x) ዛፍ ፡ እንኳ ፡ ቢቆረጥ ደግሞ ፡ ሊያቆጠቁጥ ፡ አዲስን ፡ ቅርንጫፍ ሊያበቅል ፡ ተስፋ ፡ አለው ለፍጥረት ፡ የመታደስን ይህ ፡ እንደገና ፡ ተስፋን ፡ ሰጠኸው ለእኔማ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ የነፍሴ ፡ ተስፋ የምትበልጥ ፡ ለማቆጥቆጤ ከውኃ ፡ ሸታ የክፉ ፡ ምሳር ፡ ቆርጦ ፡ :ሊጥለኝ እስከወዲያኛው ፡ ከአንተ ፡ ሊለየኝ ስመታ ፡ ተንገዳግጄ ስደርስ ፡ ወደታች ፡ ስቧጥጥ ሲብስ ፡ ማቃሰት ፡ ሆኖብኝ ፡ አንዳች ሲሸተኝ ፡ የመገኘትህ ፡ የአንተ ፡ መዓዛ ቆማለሁ ፡ ዳግም ፡ በጽኑ ፡ ምህረት ፡ ሲበዛ (፪x) አዝ፦ አልደርቅም ፡ አልደርቅም ፡ ሕያው ፡ ምንጭ አንተ ፡ አለኸኝ ፡ ኢየሱስ (፪x) በድርቅ ፡ ዘመን ፡ ከቶ ፡ እንዳልሰጋ ፍሬ ፡ ማፍራቴን ፡ ላይቆም ፡ አንዱ ፡ ጋር እምነቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መታመኛዬ ሙቀት ፡ ሲመጣ ፡ ላይፈራው ፡ ልቤ ከአንተ ፡ አጠገብ ፡ ተተክያለሁ ስለዚህ ፡ ሕይወቴ ፡ ሁሌ ፡ ለምለም ፡ ነው (፪x) ሁሌ ፡ ለምለም ፡ ነው ለመልማለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.