Loading
ደመና ፡ ሆኖብኝ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ጨልሞብኝ ዐይኖቸን ፡ አቅንቸ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ፍረድልኝ ፡ አልኩኝ (ለካ ፡ ደመናው ፡ ውኃ ያዘለ ፡ ነበር ፡ ደረቀ ፡ ባልኩበት ፡ ዝናቡ ፡ ወረደበት) (፪x) አዝ፦ ነገር ፡ ለበጐ ፡ ሆኖ ፡ አየሁኝ ፡ ነገረ ፡ ለበጐ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አውርዶ እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አግንኖ ፈተናው ፡ አዝሎኝ ፡ ለመውደቅም ፡ ስንገዳገድ ፡ ባሕሩን ፡ ሲከፍለው ፡ በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ አገኘሁኝ ፡ መንገድ አምላክ ፡ እንደሌለው ፡እንደማንም ፡ ለቆጠረኝ የምመስክረው ፡ ምናገረው ፡ አለኝ (፪x) ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ ሚያደርግ ፡ ነው እኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ሁሉ ፡ የተቻለው ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ ሚያደርግ ፡ ነው እኔስ ፡ ጋሻ፡ አለኝ ፡ሁሉ ፡ የምተማመነው የምተማመነው ፡ ተስፋ ፡ የማደርገው ፡ ነገሬን ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አርጐ ፡ ስሪ ፡ ነው ያማልክቶቻ ፡ አምላክ ፡ እምላኬ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው በዘመናት ፡ መሃል ፡ ጉልበቱ ፡ ያልዛለው ቅን ፡ ይፈርዳል ፡ ለተጠጋው ፡ በጊዜው ፡ ደርሶ ማባበልን ፡ ያውቃል ፡ የፈሰሰን ፡ እንባን ፡ አብሶ የእኔ ፡ጌታ ፡ ለአኔ ፡ ምርኮዬን ፡ መልሶ እንደገና ፡ አቆመኝ ፡ ጉልበቴን ፡ አድሶ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ምርኮዬን ፡ መልሶ እንደገና ፡ አቆመኝ ፡ ሕይወቴን ፡ አድሶ አዝ፦ ነገር ፡ ለበጐ ፡ ሆኖ ፡ አየሁኝ ፡ ነገረ ፡ ለበጐ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አውርዶ እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አግንኖ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.