Loading
በዓለም ፡ ላይ ፡ ቢዞር ፡ ቢዞር አይገኝም ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር መደነቅ ፡ መገርም ፡ ሞላብኝ አምላኬን ፡ ሳስበው ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ብቻ (፬x) ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x) ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም በጥላ ፡ መዘዋወር ፡ አያውቅም ታማኝ ፡ እንደሆነ ፡ ይኖራል የሚታመኑትን ፡ ያኮራል (፪x) አዝ፦ እርሱ ፡ ብቻ (፬x) እርሱ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x) የሚከፍት ፡ ሚዘጋ ፡ የሌለው ሚዘጋም ፡ የሚከፍትም ፡ የሌለው ሁሉን ፡ ማድረግ ፡ ፍጹም ፡ የቻለ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ብቻ (፬x) ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነው (፫x) እርሱ ፡ ብቻ ፡ አዳኝ ፡ ነው (፫x) ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.