Loading
አምላኬ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት ፡ ለአንተ ፡ እሰዋለሁ አምላኬ ፡ ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ትቼ ፡ እኔ ፡ እዘምራለሁ (፪x) አይጓደልብህ ፡ ምሥጋናዬ ፣ አይጓደልብህ ፡ አምልኮዬ(፪x) በሰልፉ ፡ መሃል ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x) ሃዘን ፡ ለቅሶዬን ፡ ትቼ ፡ እዘምራለሁ (፪x) እዘምራለሁ (፬x) በጭካኔ ፡ በትር ፡ በብዙ ፡ ቆሳስለው ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ እስር ፡ ቤት ፡ ተጥለው ጸጥታው ፡ ይሰፍናል ፡ ወትሩም ፡ ሲሆን ፡ ሌሊት ያኔ ፡ ግን ፡ ይሰማል ፡ ቁስለኛው ፡ ሲያቃስት ይጠበቅ ፡ ነበር ፡ ማቃሰታቸው ግን ፡ ተቀየረ ፡ ሌሊት ፡ ድምጻቸው ሁኔታን ፡ ትተው ፡ ሲያመሰግኑ የጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታየ ፡ ማዳኑ ዘምር ፡ ዘምር ፡ ይለኛል ፡ ኢየሱስን ፡ ሳስበው አመስግነው ፡ ይለኛል ፡ ኢየሱስን ፡ ሳስበው (፪x) ምሥጋናዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና አምልኮዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና ዝማሬዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና (፪x) ንጉሥ ፡ እዮሳፍጥ ፡ ጠላቶች ፡ ከበውት ንግስናውን ፡ ሊሽሩ ፡ እርስቱን ፡ ሊነጥቁት የአባቶቹ ፡ አምላክ ፡ ፊቱን ፡ ቢፈልገዉ ሰልፍ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ልቡን ፡ አሳረፈዉ ምሥጋናን ፡ ይዞ ፡ ወጣ ፡ አደባባይ ድልን ፡ አገኘ ፡ በጠላቱ ፡ ላይ የአምላክ ፡ ድብቅ ፡ ጦር ፡ ተንቀሳቀሰ ጠላት ፡ እርስ ፡ በእርስ ፡ ተጨራረሰ አላወራውም ፡ የጠላቴን ፡ ሰልፍ ፡ ሃይለኛ ፡ ብዬ አላወራውም ፡ አላስተጋባም ፡ ምሥጋናን ፡ ጥዬ (ልማዴ ፡ ነው) ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ለአንተ ፡ መጨመር (ልማዴ ፡ ነው) ፡ ሁኔታን ፡ ትቶ ፡ ለአንተ ፡ መዘመር (ባህሌ ፡ ነው) ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ መጨመር (ባህሌ ፡ ነው) ፡ ሁኔታን ፡ ትቶ ፡ ለአንተ ፡ መዘመር ልማዴ ፡ ነው (፪x) ባህሌ ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.