Loading
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው ትልቅ ፡ ነው ፡ እኩያ ፡ የሌለው (፪x) አዝ፦ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ ፣ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ (፬x) በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ይተቀመጠው የአባቶቼ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነዉ (፪x) እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው እኩያ ፡ የለው ፡ አምሳያ ፡ የለው ብዙዎች ፡ ነበሩ ፡ አንቱ ፡ የተባሉ በአስቀመጡት ፡ ታሪክ ፡ ዛሬ ፡ ይወሳሉ ትዝታቸው ፡ ቀረ ፡ ነበሩ ፡ ተብለው የትላንት ፡ ደማቆች ፡ ዛሬ ፡ ታሪክ ፡ ሆነው (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ዝናው ፡ አይቀዘቅዝ (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ስራው ፡ የማይነቅዝ (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ በክብር ፡ ይኖራል (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ሁሉንም ፡ ይገዛል ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ ሃያል ፡ ነዉ ፡ ከሃያላን ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ ብርቱ ፡ ነው ፡ ከብርቱዎች ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ አዝ፦ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ ፣ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ (፬x) በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ይተቀመጠው የአባቶቼ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነዉ (፪x) ጽኑሃን ፡ ሃያላን ፡ የምድር ፡ ነገሥታት መንግሥታቸው ፡ ሲወድቅ ፡ ባላሰቡት ፡ ሰዓት ግብራቸው ፡ ሲዋረድ ፡ ሲሻር ፡ ሹመታቸው ትዝታን ፡ ታቅፈው ፡ ሁሉም ፡ ሲከዳቸው (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ መንግሥቱ ፡ ዘለዓለም (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የሚተካው ፡ የለም (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የሚመስለው ፡ ማነው (የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ነው ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ ሃያል ፡ ነዉ ፡ ከሃያላን ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ ብርቱ ፡ ነው ፡ ከብርቱዎች ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ ሃያል ፡ ነዉ ፡ ሃያል ሃያል ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.