Loading
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x) ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x) ሰው ፡ በልቶ ፡ ጠጥቶ ፡ ለብሶ ፡ ተሽሞንሙኖ በየአደባባዩ ፡ ሚዛን ፡ ደፍቶ ፡ ቀኑ ነፍሱ ፡ ግን ፡ ተራቁታ ፡ ከስታና ፡ መንምና ነገሮች ፡ ቢሟሉም ፡ እርካታ ፡ ቢስ ፡ ሆና ለእኔ ፡ ግን ፡ የውጪው ፡ አይደለም ለእኔ ፡ ግን ፡ ቀዳሚው ፡ ናፍቆቴ ለእኔ ፡ ግን ፡ የፊትህ ፡ ብርሃን ለእኔ ፡ ግን ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ድምቀቴ ለእኔ ፡ ግን ፡ ቁስ ፡ አይተካልኝም ለእኔ ፡ ግን ፡ አይሆነኝ ፡ እርካታ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ አብርሆትህ ለእኔ ፡ ግን ፡ የዘመኔ ፡ ደስታ አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x) ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x) አልናፍቀውም ፡ የዚን ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ ዝና አልናፍቀውም ፡ ጠፊ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ ፡ ጌታ አልናፍቀውም ፡ አንተን ፡ ትቶ ፡ መኖር ፡ ለአፍታ አልናፍቀውም ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ በየትኛውም ፡ ስፍራ ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ቁም ፡ ነገር ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ መኖር ፊትህ ፡ ይብራልኝ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ ከምንም ፡ በላይ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ በሌለህበት ፡ አይሁን ፡ ኑሮዬ መገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ መሰማሪያዬ ነፍስን ፡ ሊያስደስቷት ፡ ቢበሉ ፡ ቢጠጡ በሹመኞች ፡ ወንበር ፡ ደግሞም ፡ ቢቀመጡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ፍላጐት ፡ መች ፡ በዚህ ፡ ይረካል የያዘውን ፡ ጠግቦት ፡ ኋላ ፡ ሌላ ፡ ያምረዋል ለእኔ ፡ ግን ፡ የዚች ፡ ዓለም ፡ መልኳ ለእኔ ፡ ግን ፡ ጠፊ ፡ ነው ፡ ገብቶኛል ለእኔ ፡ ግን ፡ ውስጤም ፡ አይሳሳለት ለእኔ ፡ ግን ፡ ፍቅርህ ፡ በልጦብኛል ለእኔ ፡ ግን ፡ መኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ለእኔ ፡ ግን ፡ ከምንም ፡ ይበልጣል ለእኔ ፡ ግን ፡ የማያልፍ ፡ ምርጫ ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ውለህልኛል አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x) ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.