Loading
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ጭው ፡ ባለው ፡ በረሃ አጋር ፡ ከነልጇ ፡ ወደዚያ ፡ ተሰዳ ተደፍታ ፡ ስታለቅስ ፡ ምርር ፡ ያለ ፡ ለቅሶ ምንጭ ፡ አፈለቀላት ፡ እግዚአብሔር ፡ ደርሶ [1] ይደርሳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይደርሳል ይደርሳል ፡ የተጠማ ፡ ያያል ምንጭን ፡ ያፈልቅና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x) መጠጥ ፡ እነደጠጣች ፡ ስካር ፡ እንደያዛት ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ እንኳን ፡ ሃናን ፡ ጠረጠራት እርሷ ፡ ግን ፡ የውስጧን ፡ ችግሯን ፡ ለሚያውቀው ተናገረችና ፡ ልቧ ፡ በእርሱ ፡ ፀና [2] ይረዳል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይረዳል ይረዳል ፡ የውጥን ፡ ይረዳል የተዘጋን ፡ ከፍቶ ፡ በልጅ ፡ ይባርካል (፪x) እስራኤላውያኖች ፡ ቀንበር ፡ ከብዶባቸው የግብፅ ፡ ባርነት ፡ እጅግ ፡ ሰልችቷቸው ጮሁ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዲታደጋቸው እጁን ፡ ዘረጋና ፡ ነፃ ፡ አወጣቸው [3] ያወጣል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያወጣል ያወጣል ፡ ነፃነት ፡ ይሰጣል ከእስራት ፡ ይፈታል ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x) እመሰክራለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ ንብ ፡ ማርን ፡ እንዲከብ ፡ ተከብቤ ፡ ሳለሁ በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ አምላኬን ፡ ስጣራ እርሱም ፡ ደረሰልኝ ፡ ጨለማዬም ፡ በራ ያበራል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያበራል ያበራል ፡ ጨለማን ፡ ይገፋል በድንቅ ፡ ይደርስና ፡ አሜን ፡ ያሳርፋል (፪x) ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ ለሊትም ፡ በእሳት አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ መምራትን ፡ ሲያውቅበት ላዘነው ፡ መፅናናት ፡ ለደካማው ፡ ብርታት ይሄ ፡ ነው ፡ አምላካችን ፡ እስኪ ፡ ዕልል ፡ በሉለት ይብዛለት ፡ አሁንም ፡ ይብዛለት ይብዛለት ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት አሜን ፡ ለአምላካችን ፡ ክብር ፡ ይሁንለት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.