Loading
አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x) የሰው ፡ ድካሙ ፡ ለሥጋ ፡ ሆኖአል አይ ፡ ነፍሱ ፡ ግን ፡ በርሃብ ፡ ጠውልጓል ያከማቻውም ፡ ለሌላ ፡ ይሆናል የደከመበትን ፡ ሳይበላ ፡ ይቀራል (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x) ፈጣሪህን ፡ አስብ ፡ በጉብዝናህ ፡ ወራት ኃይል ፡ ከአንተ ፡ እርቆ ፡ ሳይጥልህ ፡ ጉልበት ትእዛዙን ፡ ጠብቅ ፡ ፍራ ፡ እግዚአብሔርን ነፍስህ ፡ ሳይመለስ ፡ ሥጋ ፡ ወደ ፡ አፈር (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x) በሕይወት ፡ ዘመንህ ፡ የሚሻልህን እንዳትረዳው ፡ ጋርዶ ፡ የያዘህን ዓይንህ ፡ ይገለጥ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ሁሉ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በሙሉ በሕይወት ፡ ዘመንሽ ፡ የሚሻልሽን እንዳትረጂው ፡ ጋርዶ ፡ የያዘሽን ዓይንሽ ፡ ይገለት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ከኢየሱስ ፡ ውጭ ፡ ያለው ፡ በሙሉ አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.