Loading
እግዚአብሔር ፡ እሩህሩህና ፡ መሃሪ ፡ ነው ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ለሚታገሱት ፡ ሁሉ ፡ ቸር ፡ ነው ምህረቱም ፡ በስራው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነው አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፪x) ስለ ፡ ነገሠ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ከፍ ፡ ከፍ ፡ ስላለ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ግርማው ፡ ስለሚያስፈራ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ሥሙ ፡ ታላቅ ፡ ስለሆነ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፪x) ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካሉ አፍም ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ያቀርባሉ መላእክት ፡ በሰማይ ፡ ለክብሩ ፡ ያዜማሉ ቅዱሳን ፡ በናፍቆት ፡ በምድር ፡ ይቀኛሉ አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.