Loading
በዓለም ፡ ጨለማ ፡ እውር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ አንድ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይኔን ፡ ከፍቶት ፡ አየሁ (፫x) አንድ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይኔን ፡ ከፍቶት ፡ አየሁ ብርሃኔ ፡ ተገፎ ፡ በዓለም ፡ ስደናቀፍ ዓይኔን ፡ ከፈተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፫x) ዓይኔን ፡ ከፈተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳሙ ፡ ይክበር ከጉዳት ፡ የሚያድን ፡ መሪ ፡ እንኳን ፡ ሳይንረኝ አንድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እረዳት ፡ ሆነልኝ (፫x) አንድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እረዳት ፡ ሆነልኝ ከጥንት ፡ ከበፊቱ ፡ እውር ፡ እንደነበርኩ አሁን ፡ ግን ፡ እንደማይ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፪x) አሁን ፡ ግን ፡ እንደማይ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ ከሸንጐም፡ ብወጣ ፡ በማንም ፡ ብጠላ ጌታን ፡ አመልካለሁ ፡ የሕይወቴን ፡ ከለላ (፫x) ጌታን ፡ አመልካለሁ ፡ የሕይወቴን ፡ ከለላ ጠቃሚና ፡ ጐጂውን ፡ የማላውቅ ፡ ለይቼ ብርሃኔ ፡ ተገልጦ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ አይቼ (፫x) ብርሃኔ ፡ ተገልጦ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ አይቼ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.