Loading
አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x) የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ ሰውማ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ያው ፡ እንደተፈጥሮ ድጋፍን ፡ ረዳትን ፡ ፈላጊ ፡ ነው ፡ ምርኩዝን ስለዚህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መጠጋት ፡ ያዋጣል የታመነ ፡ አንተን ፡ ድል ፡ በድል ፡ ይሆናል አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x) የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ ትመረምራለህ የሰውን ፡ ሁለንተና ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ታውቃለህ በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ አንደአንተ ፡ ማን ፡ አለ ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ ነህ ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ ፡ ኤሄሄ ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፪x) አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x) የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ መምራትን ፡ ታውቃለህ ሌሊትም ፡ በእሳት ፡ ጌታ ፡ ትመራለህ ልዩ ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ጥበቃህ ተመስገን ፡ ተባረክ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x) የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ የምታስመካ ፡ ጌታ ፡ የምታኮራ ፡ ሆሆሆሆ የምታስመካ ፡ ጌታ ፡ የምታኮራ ፡ አሃ (፪x) ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፪x) ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.