Loading
አበርትቶኛል ፡ ጉልበቴ ፡ እጅግ ፡ ዝሎ አሻግሮኛል ፡ ዮርዳኖስን ፡ ከፍሎ እንዴት ፡ እረሳዋለሁ ፡ እግዚአብሔርን ከበረት ፡ አውጥቶ ፡ ከግብጽ ፡ ያወጣኝን አዝ፦ ላመስግነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) አስቀድሞ ፡ አውቆኛል ፡ በሆድ ፡ ሳልሰራ መርጦኛል ፡ እራሱ ፡ ጨለማዬም ፡ በራ ዓይኖቼም ፡ ማዳኑን ፡ እዩ ፡ ተዓምራቱን ስለ ፡ ፍቅርም ፡ ብሎ ፡ የሰዋውን ፡ ልጁን አዝ፦ ላመስግነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) አስጨናቂዎቼ ፡ ሰልፍ ፡ አብዝተውብኝ ከአምላኬ ፡ ጉያ ፡ መስሏቸው ፡ የሚነጥቁኝ ግን ፡ የማያንቀላፋው ፡ ተግቶ ፡ የሚጠብቀኝ በዙሪያዬ ፡ ካሉት ፡ በእውነት ፡ አሳረፈኝ አዝ፦ ላመስግነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ በፍቅሩ ፡ ይዞኛል እንዳልወድቅም ፡ ምርኩዝ ፡ ድጋፍ ፡ ሆኖልኛል ምን ፡ ልበለው ፡ እኔስ ፡ ውለታው ፡ በዛብኝ ሕያዋን ፡ ሁላችሁ ፡ እስኪ ፡ አመስግኑልኝ አዝ፦ ላመስግነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x) ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.