Loading
አዝ፦ ክበር ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ጠገብኩ ንገሥ ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ረካሁ (፪X) ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ) ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ) እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x) አይኔ ፡ በርቶ ፡ ሁሉን ፡ አይቶ ቢናገር ፡ ውስጤ ፡ መቼ ፡ እረክቶ አልጠገብኩም ፡ አልረካሁም ክብሬን ፡ ትቼ ፡ ክበር ፡ አልኩህ (፪x) ይክበር ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ እንጂ ያገኘሁት ፡ ሰላም ፡ በዚህ ፡ ወዳጅ ይክበር ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ እንጂ ያገኘሁት ፡ እረፍት ፡ በዚህ ፡ ወዳጅ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ሲወዳደር ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ተሰርቶልኝ ፡ የእኔ ፡ ሥራ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ሌት ፡ እና ፡ ቀን ፡ ብዘምር (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ኑሮዬ ፡ ሆኖ ፡ የተአምር (፪x) ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ) ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ) እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x) ላለው ፡ በሰማይ (ሌላ) ከሰው ፡ ለሚለይ (ሌላ) ከምለው ፡ በላይ (ሌላ) ሌላ ፡ አምልኮ (ሌላ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃሃ) ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x) ላለው ፡ በሰማይ (ሌላ) ከሰው ፡ ለሚለይ (ሌላ) ከምለው ፡ በላይ (ሌላ) ሌላ ፡ አምልኮ (ሌላ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃሃ) ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x) አዝ፦ ክበር ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ጠገብኩ ንገሥ ፡ ብዬ ፡ መቼ ፡ ረካሁ (፪X) ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (አሃሃ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ) ያንተን ፡ ፍቅር ፡ ምህረት (አሃሃ) እኔ ፡ ምገልፅበት (፪x) (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ እኔስ ፡ ባወራ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለእጅህ ፡ አሻራ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ ትተህልኝ (ብዙ ፡ አይደለም) ፡ ክብሬን ፡ ብጥል ፡ ሰው ፡ እያየኝ አምልኮ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ክብርም ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ስግደቴ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ለእርሱ ፡ ብቻ (ለእርሱ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ) ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x) አምልኮ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ክብርም ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ስግደቴ ፡ ለእርሱ (ለእርሱ) ለእርሱ ፡ ብቻ (ለእርሱ) ምነው ፡ በኖረና (አሃሃ) ለአንተ ፡ ክብር ፡ ዝና (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.