Loading
አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x) የሳቁ ፡ ነበሩ ፡ በአንተ ፡ ስታመን ትፈታዋለህ ፡ ስል ፡ እንቆቅልሼን ጠላቴም ፡ ወዳጄም ፡ ስታስበኝ ፡ አዩ የሚያመልከው ፡ አምላክ ፡ ለካ ፡ ይሰማል ፡ አሉ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x) ቃልህን ፡ አምናለሁ ፡ አይደለም ፡ ስሜቴን እንደምትሞላው ፡ መሻቴን ፡ የውስጤን ፍፃሜና ፡ ተስፋ ፡ የምትሰጠዉ ሃሳብህ ፡ ይበልጣል ፡ እጠብቃለሁ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x) በአንተ ፡ እታመናለሁ ፡ አልነዋወጥም ወደ ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ አማራጭ ፡ አላይም ግድ ፡ ይልሃልና ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ነገር ከአንተ ፡ እጠብቃለሁ ፡ ወደሌላው ፡ ሳልዞር (፪x) አንተን ፡ ብቻ ፡ እጠብቃለሁ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህና ለዘላለም ፡ የሚያጸና (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.