Loading
ኤልሻዳይ ፡ ብዬ ፡ ዘምሬአለሁ ጌታም ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ መስክሬአለሁ አሁን ፡ ግን ፡ ቃላትን ፡ ስላጣሁ ከምለው ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ ከምልህ ፡ በላይ ፡ ጌታ (፫x) ፡ ነህ የእኔ ፡ ቃላት ፡ የማይገልጽህ ፡ የሰው ፡ ቃላት ከምልህ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ ነህ እኔን ፡ አሳፍሮኝ ፡ አያውቅም ፡ የማገለግለው ፡ ጌታ ያኖረኛል ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ጠላቶቼን ፡ እየመታ ለምን ፡ ይህን ፡ አደረግህ? ብሎ ፡ የጠየቀው ፡ የለም ሥልጣኑ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ጉልበቱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው እሠይ (፮x) ጌታ ፡ ነው ፡ በምድር ፡ በሰማይ ከሁሉም ፡ በላይ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ በሰማይ ከሁሉም ፡ በላይ ስለ ፡ በደሌ ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ መስቀል ፡ ተሸክም ፡ ያየው ፡ ሰው የሰማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ማን ፡ ይገምተው? ቢሆንም ፡ ተነሥቶ ፡ ጌታ ፡ በዓብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀምጧል በሰማይና ፡ በምድር ፡ ሁሉን ፡ አንበርክኳል ግንበኞች ፡ የናቁት ፡ ድንጋይ ፡ እርሱ ፡ የማዕዘን ፡ ራስ ፡ ሆነ አይጠቅምም ፡ ብለው ፡ የጣሉት ፡ የትንሣዔ ፡ ጌታ ፡ ሆነ የናቁትን ፡ አሳፍሮ ፡ እጅ ፡ አስጭኗቸዋል በመንግሥቱም ፡ እያበራ ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.