Loading
እኔ ፡ ያልዘመርኩ ፡ ማን ፡ ይዘምር? ለኢየሱሴ ፡ ሥሙ ፡ ክብር ስንቴ ፡ ከሞት ፡ አምልጫለሁ? ሲታደገኝ ፡ አይቻለሁ እንደ ፡ እኔ ፡ ምሕረት ፡ የበዛለት ምሥጋናውን ፡ ይሰዋለት የታሪኬ ፡ ጅማሬና ፡ የፍጻሜ ፡ መደምደሚያው በሕይወቴ ፡ ሥፍራ ፡ ያለው ፡ አንድ ፡ ቁጥር ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው በቁልምጫ ፡ የምጠራው ፡ ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ነክቶት ፡ ነው በደም ፡ ተለውሼ ፡ ሲያየን ፡ ፊቱን ፡ ዞሮ ፡ ያላለፈኝ ጠርቶ ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ፡ ምሕረቱን ፡ ያበዛልኝ እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ አለና ፡ ነው? ከማመስገን ፡ የምዘገየው ይህን ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት መንገድ ፡ ዳር ፡ ወድቄ ፡ ሲያየኝ ፡ ራርቶ ፡ በፍቅር ፡ ያኖረኝ ቸርነቱ ፡ በዝቶ ፡ እስኪታይ ፡ ሰማይን ፡ ከፍቶ ፡ በእኔ ፡ ላይ ወደ ፡ ራሱ ፡ ስላስጠጋኝ ፡ እንዳልዘምር ፡ ማነው ፡ ከልካይ? ይህን ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት አምላኬ ፡ ነህ ፡ አልኩት በዘመኔ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ አይቻለሁ እግዚአብሔርን ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ ባሕር ፡ ከፍሎ ፡ ሲያሻግረኝ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል እግዚአብሔርን ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብሎታል በዘመኔ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ አይቻለሁ እግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ ሲሸከመኝ ፡ ሲታገሰኝ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል እግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ብሎታል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.