Loading
አዝ፦ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ አስደናቂነትህን ፡ አይተን ፡ እስከዛሬ እንጂ ፡ መቼ ፡ ኖርን? ሰምተን ፡ ጭፍን ፡ ወሬ ሥራህን ፡ በሕይወታችን ፡ ተገልጦ ፡ ስላየነው አናፍርም ፡ ያኮራል ፡ የአንተ ፡ መሆን ፡ ክብር ፡ ነው አዝ፦ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ ቃላት ፡ አጣሁ ፡ እንጂ ፡ ብዙ ፡ እናገር ፡ ነበር ጠላት ፡ በእኔ ፡ ዘግቶ ፡ ስለከፈትክልኝ ፡ በር ርስት ፡ አገኘሁ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዚህ ፡ አበቃ? በቤትህ ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ ቀረና ፡ ሰቆቃ አዝ፦ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ ለእኔ ፡ አጋዥ ፡ የሚሆን ፡ ጠፍቶ ፡ ዝም ፡ ሲባል ረዳቴ ፡ ሆነኸኝ ፡ ከተፍ ፡ ብለሃል የቀራንዮ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ፡ ዘለዓለም የክፉ ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም አዝ፦ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ሃሌሉያ ፡ አሃ ፡ ሃ ድንቅ ፡ ነህ (፬x) ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.