Loading
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ አሮጌውን ፡ በአዲስ ፡ ተክቶ እስኪወስደኝ ፡ ጌታዬ ፡ መጥቶ የሞተልኝ ፡ ወዳጄን ፡ እስካይ ናፍቆቴ ፡ እስኪፈጸም ፡ በሰማይ እንዲጠብቀኝ ፡ ምድር ፡ ላይ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ በሙሉ ልኖር ፡ እኔም ፡ እንደ ፡ ሕያው ፡ ቃሉ ምኞቴ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ አንድ ፡ ነገር እስካለሁ ፡ በዚህች ፡ ጠፊ ፡ ምድር ይህን ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ የመምጫህን ፡ ቀን ፡ ስለማላውቅ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተን ፡ መገለጥ ያለ ፡ ነውርና ፡ ነቀፋ ሆኜ ፡ እንድጠብቀው ፡ በተስፋ ይህን ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንድን ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ ያንን ፡ ከእጁ ፡ እናፍቃለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.