Loading
በምሥጋና ፡ ወደመቅደሱ ፡ እገባለሁ ከልቤ ፡ ሆኜ ፡ እቀኛለሁ ያከበረኝን ፡ ሰው ፡ ያረገኝን አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ በምሥጋና ፡ ወደመቅደሱ ፡ እገባለሁ ከልቤ ፡ ሆኜ ፡ እቀኛለሁ የወደደኝን ፡ አዎ ፡ የሞተልኝን ኢየሱሴን ፡ አከብረዋለሁ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ኢየሱሴ ፡ ክብሬ ፡ ማረጌ ኢየሱሴ ፡ የአብ ፡ ስጦታ ኢየሱሴ ፡ ነህ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ኢየሱሴ ፡ ውበቴ ፡ ጌታ ኢየሱሴ ፡ የምትወደድ ኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ኢየሱሴ ፡ አሳዳጊዬ ኢየሱሴ ፡ ይቧረክ ፡ ስምህ (፪x) የሚያንኳኳ ፡ መልስ ፡ ሽቶ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተን ፡ ጠርቶ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተን ፡ ጠርቶ (፪x) ልመናውን ፡ ሰማህለት ፡ ሸክሙን ፡ አንተ ፡ ወሰድክለት ሸክሙን ፡ አንተ ፡ ወሰድክለት (፪x) ተደንቂያለሁ ፡ በማዳንህ ተነገሮ ፡ አያልቅም ፡ ድንቅ ፡ ስራህ መፍቻው ፡ ተገኝቶ ፡ የእንቆቅልሹ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኗል ፡ ዮሴፍ ፡ ትንሹ ተዐምር ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ ድንቅ ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ ከፍ ፡ በል ፡ በምሥጋናዬ (፪x) የቱን ፡ ትቼ ፡ የቱን ፡ ላውራ ኢየሱሴ ፡ የአንተን ፡ ስራ (፪x) ባይመጥንም ፡ ምሥጋናዬ ይኸውልህ ፡ አባብዬ (፪x) ሰው ፡ የናቀውን ፡ የገፋውን ፡ መቼ ፡ ተውከው ፡ ብቸኛውን መቼ ፡ ተውከው ፡ ብቸኛውን (፪x) አከበርከው ፡ በአደባባይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጣለት ፡ ከሠማይ ትዕዛዝ ፡ ወጣለት ፡ ከሠማይ (፪x) አይቻለሁኝ ፡ ስትረዳ ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ለተጐዳ እጄን ፡ በእጆችህ ፡ ይዘህ ፡ መራህ ያልገመትኩትኝ ፡ ክብር ፡ አሳየኸኝ ማረጌ ፡ ክብሬ ፡ ኢየሱሴ ላምልክህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ ማረጌ ፡ ክብሬ ፡ ኢየሱሴ ላድንቅህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ ላምልክህ ፡ ከልቤ ፡ ኢየሱሴ ላምልክህ ፡ ከልብ ፡ ከነፍሴ ኢየሱሴ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ ኢየሱሴ ፡ መታመኛዬ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ውዴ ኢየሱሴ ፡ ወንድም ፡ ጋሻዬ ኢየሱሴ ፡ ምትክም ፡ የለህ ኢየሱሴ ፡ የፍቅር ፡ ምርጫዬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.