Loading
በምድራዊው ፡ ጥቅም ፡ ነፍሱ ፡ ያልታሰረ ክቡሩን ፡ አደራ ፡ በስራ ፡ ያዋለ እራሱን ፡ ሸሽጐ ፡ አምላኩን ፡ ሚያሳይ ማነው ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ እውነተኛ ፡ አገልጋይ (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ታማኝ ፡ አገልጋይ ፤ ማነው ፡ ትጉህ ፡ ኧረኛ ማነው ፡ ልባም ፡ መጋቢ ፤ ማነው ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ማነው ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ ፤ ማነው ፡ ደግሞም ፡ የጸሎት ፡ ሰው ማነው ፡ ለነፍሳት ፡ አሳቢ ፤ ማነው ፡ እውነት ፡ የሚገደው እንዲህ ፡ ሲያደርግ ፡ ለሚገኘው ከአምላኩ ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ ፡ አለው ከጊዜያዊው ፡ ይልቅ ፡ ሚበልጠውን ፡ ሽቶ ዘለዓለማዊውን ፡ ከሩቅ ፡ ተመልክቶ ትኩር ፡ ብሎ ፡ ያየ ፡ ያንን ፡ ብድራቱን በጌታው ፡ ያረፈ ፡ እውነተኛ ፡ ካህን (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ታማኝ ፡ አገልጋይ ፤ ማነው ፡ ትጉህ ፡ ኧረኛ ማነው ፡ ልባም ፡ መጋቢ ፤ ማነው ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ማነው ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ ፤ ማነው ፡ ደግሞም ፡ የጸሎት ፡ ሰው ማነው ፡ ለነፍሳት ፡ አሳቢ ፤ ማነው ፡ እውነት ፡ የሚገደው እንዲህ ፡ ሲያደርግ ፡ ለሚገኘው ከአምላኩ ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ ፡ አለው ነውረኛውን ፡ ነገር ፡ ጸያፉን ፡ የናቀ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ዝና ፡ እራሱን ፡ ያራቀ ቅድስናን ፡ ለብሶ ፡ ለጌታው ፡ የሚኖር እግዚአብሔር ፡ የጠራው ፡ ማነው ፡ አምባሳደር (፪x) እርዳኝ ፡ አባቴ ፡ ኦሆሆሆሆ አግባኝ ፡ ከቤቴ ፡ በሰላም (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.