Loading
ክብር ፡ ያስመለሱ ፡ መሰውያን ፡ ያደሱ ሁሉም ፡ የረሱትን ፡ በእድሜያቸው ፡ ያነሱ እግዚአብሔርን ፡ ሽተው ፡ ታሪክ ፡ ያስለወጡ በየዘመናቸው ፡ ለእውነት ፡ የተሰጡ ነበሩ ፡ አምላካቸውን ፡ ፈገግ ፡ ያስደረጉ ከእጁ ፡ ይልቅ ፡ ፊቱን ፡ ለልብ/ከምር ፡ የፈለጉ (፪x) በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ሌላ ፡ አልሻም አንተን ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ ሌላ ፡ አላሳድድም በልቤም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ አይቀመጥም ለአንተ ፡ እንጂ ፡ አምላኬ ፡ ለማንም ፡ አይሆንም ብዙዎች ፡ ረክተዋል ፡ የእጅህን ፡ ስራ ፡ አይተው እንጀራም ፡ ተርበው ፡ ስላበላሃቸው በከንቱ ፡ ፈለጉህ ፡ ደግመህ ፡ እንድጸጣቸው በቃኝ ፡ በማያውቀው ፡ ከንቱ ፡ መሻታቸው እኔ ፡ ግን ፡ አንዲት ፡ ነገር ፡ እለምንሃለሁ ከምትሰጠኝ ፡ በላይ ፡ አንተኑ ፡ እሻለሁ (፪x) ወደቀኝም ፡ ሳልል ፡ ወደግራም ፡ ሳላይ የመደበልኝን ፡ ተቀብዬ ፡ ከላይ ሩጫዬን ፡ እሮጣለሁ ፡ እርሱ ፡ እየመራኝ በመጨረሻው ፡ ቀን ፡ በእጣ ፡ ክፍሌ ፡ እንድገኝ ወሰንኩኝ ፡ ላልመለስ ፡ እስከመጨረሻ ከአምላኬ ፡ በስተቀር ፡ ልቤም ፡ ሌላ ፡ አይሻ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.