Loading
ዓይኖቼን ፡ ወደተራሮች ፡ ባቀና ረዳቴ ፡ ይመጣል ፡ ብዬ ፡ ደጅን ፡ ብጠና ግን ፡ ተራራዎች ፡ መልስን ፡ ሰጡኝ ፡ በዝምታቸው ሚስጥሩ ፡ ገባኝ ፡ እነርሱም ፡ እርዳታ ፡ እንደሚያሻቸው ከታራራውም ፡ ላይ ፡ አሻቅቤ ፡ ሳይ ፡ በላይ ፡ በሠማይ ረድኤቴ ፡ መጣ ፡ እይተራመደ ፡ በደመናት ፡ ላይ እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ እንደሌለ ፡ ይህንን ፡ ስላየሁ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ መኖሪያዬ ፡ አድርጌዋለሁ (፪x) እንደተፈታች ፡ ሚዳቋ ፡ እንደተፈታች እንደተፈታች ፡ እምቦሳ ፡ እንደተፈታች ልውጣ ፡ ላይ ፡ ልውረድ ፡ ታች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች ቧረቀች ፡ ፈነደቀች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች (፪x) እስቲ ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር እስቲ ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ ጌታን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር ጌታን ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሥሙ ፡ ሲወደስ ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፪x) ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ ይክበር ፡ ይክበር ፡ ይክበር ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ በእኔና ፡ በሞት ፡ መካከል ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ እርሷንም ፡ ተራምዶ ፡ ውጦ ፡ ሊያስቀረኝ ፡ እጅጉን ፡ ጓግቶ በጠላትም ፡ ሰፈር ፡ በቃ ፡ ሽንፈቴ ፡ ተረጋገጠ ግን ፡ ረዳቴ ፡ መጣ ፡ በቅጽበት ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ ሊሰለጥንብኝ ፡ ባለው ፡ ቀን ፡ ጠላቴ ፡ ሰለጠንኩበት ለእኔ ፡ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ተቀበረበት ድል ፡ አድራጊው ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ እያደረገ ፡ በሰልፉ ፡ መሃል በምሥጋና ፡ ነዶ ፡ በምርኮ ፡ ብዛት ፡ ያዘምረኛል/ያዘልለኛል (፪x) እንደተፈታች ፡ ሚዳቋ ፡ እንደተፈታች እንደተፈታች ፡ እምቦሳ ፡ እንደተፈታች ልውጣ ፡ ላይ ፡ ልውረድ ፡ ታች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች ቧረቀች ፡ ፈነደቀች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች (፪x) እስቲ ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር እስቲ ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ ጌታን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር ጌታን ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሥሙ ፡ ሲወደስ ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፪x) ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፫x) ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ ይክበር ፡ ይክበር ፡ ይክበር ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.