Loading
ክፉ ፡ ሳይመጣ ፡ ከሩቅ ፡ አይተህ ለልጅህ ፡ ሚስጥርን ፡ ትገልጣለህ እንዳልጠፋ ፡ በንፋስ ፡ ማዕበሉ ትታደገዋለህ ፡ ሆነህ ፡ መርከቡን አዋቂ ፡ ነህ ፡ ሁሉንም ፡ አውቀኸዋል የጥፋትን ፡ ውኃ ፡ ሰብስበሃል የሞገዱን ፡ መናወጥ ፡ ዝም ፡ አሰኘህ ለባሪያህ ፡ መልካምን ፡ አደረግህ ብዙ ፡ ጐርፍ ፡ ተነስቶ ፡ ሕይወቴን ፡ ሊያጠፋ ዕንቁዬን ፡ ሊያስጥለኝ ፡ ሊያስቆርጠኝ ፡ ተስፋ ነፍሴን ፡ ያስጨነቀ ፡ ያናወጠ ፡ መከራ ቀስ ፡ በቀስ ፡ እየገፋ ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ተራራ በእሳት ፡ ካልነጠረ ፡ ወርቅ ፡ እንደማይደምቀው ያኔ ፡ እያስጨነቀኝ ፡ ለካ ፡ ለበጐ ፡ ነው ያረጀው ፡ የደከመው ፡ እምነቴ ፡ በፀጋህ ፡ ታድሶ በዝማሬ ፡ ተተካ ፡ የትላንቱ ፡ ለቅሶ ሃሌሉያ (፫x) ለታመነህ ፡ ሆነሀዋል ፡ መጠለያ የተመካብህ ፡ አመለጠ ፡ በአንተ ፡ ጉያ ሃሌሉያ (፫x) የታመነህ ፡ ስንቱ ፡ ዳነ ፡ በአንተ ፡ ጉያ የተመካብህ ፡ ስንቱ ፡ ዳነ ፡ በአንተ ፡ ጉያ የታመነ ፡ አመለጠ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.