Loading
አዝ፦ እወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ መች ፡ ቀረሁ ፡ ስላንተ ፡ ሰምቼ አወኩህ ፡ አንተ ፡ ተጠግቼ (፪x) አልናከኝም ፡ ተቀብለኸኛል ልጅህም ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል ኢየሱስ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሥምህን ፡ ለመጥራቴ ፡ አዎ (፪x) ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ቤትህ ፡ ለመኖሬ ፡ አዎ (፪x) በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ስትገባ መውደዴን ፡ ገለፅኩልህ ፡ በእንባ ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር ከማምለክ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ስትገባ ማፍቀሬን ፡ ገለፅኩልህ ፡ በእንባ ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር ለቃልህ ፡ ከመሸነፍ ፡ በቀር ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር አዝ፦ እወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ ለፍቅሬ ፡ መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢያጥረኝ ፡ እንኳን ግን ፡ ላወራ ፡ ልናገረው ፡ ዝም ፡ ከማለት ፡ ቢሻል የገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ እያልኩኝ ፡ ሳውራ ድንቅህን ፡ አሳየኸኝ ፡ በዘመኔ ፡ በየተራ ትገርማለህ ፡ ታስገርማለህ ትገርማለህ ፡ አንተ ትገርማለህ ፡ ታስገርማለህ ትደንቃለህ ፡ አንተ አዝ፦ እወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x) አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ አልቀረሁ ፡ ስላንተ ፡ ሰምቼ አወኩህ ፡ አንተ ፡ ተጠግቼ (፪x) አልናከኝም ፡ ተቀብለኸኛል ልጅህም ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል ኢየሱስ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ልጅህ ፡ ለመሆኔ ፡ አዎ (፪x) ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አባት ፡ ለማግኘቴ ፡ አዎ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.