Loading
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የከበርከው ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ የነበርከው (፪x) ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ የፀና እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ ገናና (፫x) ገናና ፡ ብቻህን ፡ ገናና ገናና ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ገናና ለሁሉም ፡ ምዕራፍ ፡ መጀመሪያቸው መውጣትና ፡ መግባት ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው ባለዝና ፡ ነህ ፡ ሁሉም ፡ ያውቅሃል ገናናነትህ ፡ ደግሞ ፡ ዓለምን ፡ ሞልቷል የከበረ ፡ የነገስህ ፡ ከፍ ያልህ ፡ የበረታህ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x) አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የከበርከው ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ የነበርከው (፪x) ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ የፀና እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ ገናና (፫) ገናና ፡ ብቻህን ፡ ገናና ገናና ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ገናና አማልክት ፡ ተብለው ፡ እጅግ ፡ ተፈርተው የሰዎች ፡ ሥራዋች ፡ ፍጡር ፡ ፈጥሩዋችው አይሰሙ ፡ አያዩ ፡ ደግሞ ፡ አይመልሱ ላወዳድርህ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ አንተን ፡ ከእነሱ ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ አይመለክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ አይመለክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x) ወደር ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ መሳይ ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ (፪x) ሰማይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ምድር ፡ የምትረግጥ ትላንት ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ የማትለወጥ እረጅምና ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ዙፋንህ የማይቆጠር ፡ ነው ፡ እድሜ ፡ ዘመንህ ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ አይሰበክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x) ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x) ሌላ ፡ አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ ሌላ ፡ ከብሮ ፡ አይታይም ፡ ካንተ ፡ ሌላ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነግሶ ፡ አይታይም ፡ ካንተ ፡ ሌላ ወደር ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ መሳይ ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.