Loading
ሕይወቴን ፡ ሰጥቼ ፡ ተከተልኩት የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አደረኩት ለመጪውም ፡ ዘመን ፡ እጣ ፡ ፈንታዬ ላደርገው ፡ ወሰንኩኝ ፡ ከለላዬ መላው ፡ እኔነቴን ፡ አስገዝቼ መኖር ፡ ጀመርኩኝ ፡ ተደስቼ (፪x) አዝ፦ ነፍሴ ፡ ተጓደደች ፡ አምላኳን ፡ አግኝታ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለች ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x) ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x) በተራራዎች ፡ ላይ ፡ እየዘለለ በኮረብቶችም ፡ ላይ ፡ እየተወረወረ ከፍታን ፡ ዝቅታን ፡ ሁሉ ፡ አልፎ በመሃል ፡ ያለውን ፡ አሸንፎ የውዴ ፡ ድምጽ ፡ ፈጥኖ ፡ ይመጣልኛል ከአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ ያጠግባታል (፪x) አዝ፦ ነፍሴ ፡ ተጓደለች ፡ አምላኳን ፡ አግኝታ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለች ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x) ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x) ከማር ፡ ወለላ ፡ ይልቅ ፡ ይጣፍጠኛል ሁሌ ፡ ስጠራህ ፡ ያስደንቀኛል የማዐዛው ፡ ጠረን ፡ ሽታው ፡ አውዶኝ በእርሱ ፡ ተስቤ ፡ ቤቱ ፡ ቀረሁኝ (፪x) አገልጋይ ፡ ሆንኩኝ ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.