Loading
አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል (፪x) አያለሁ ፡ አዲስ ፡ ቀን ፡ ከደመናው ፡ ማዶ ብርሃን ፡ ሲወጣልሽ ፡ ጨለማውን ፡ ቀዶ የራቁት ፡ ልጆችሽ ፡ ይሰበሰባሉ እውነትም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃያል ፡ ነው ፡ እያሉ ባማሩት ፡ መቅደሶች ፡ ወንጌል ፡ ይሰበካል ህጻን ፡ ሽማግሌው ፡ ለአምላክ ፡ ክብር ፡ ያመጣል እግዚአብሔርም ፡ ቃሉን ፡ በታምር ፡ ያጸናል ሊሰራ ፡ ሲወጣ ፡ ማን ፡ ይቃወመዋል ፡ ማን ፡ የከለክላል አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል እውቀትና ፡ ጥበብ ፡ ከአምላክ ፡ የተዋሉ ኃጢያትን ፡ ጠልተው ፡ ለጽድቅ ፡ የሚኖሩ ልዋይና ፡ ዝና ፡ ከቶ ፡ ማይገዛቸው ለፍርድና ፡ ለእውነት ፡ ቅናት ፡ የበላቸው ልጆች ፡ አሉሽ ፡ ገና ፡ ተግተው ፡ የሚነሱ ለምስኪኑ ፡ መውደቅ ፡ ከልብ ፡ የሚሳሱ የተገባልሽ ፡ ቃል ፡ በእርግጥ ፡ ይፈጸማል አምላክሽ ፡ ሊያድንሽ ፡ ሊታደግሽ ፡ ወጥቷል ፡ ሊታደግሽ ፡ ወጥቷል አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.