Loading
ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ ታሪክ ፡ አገላብጠን ሕይወትን ፡ ግራና ፡ ቀኙን ፡ ተመልክተን አንድ ፡ እውነት ፡ ተረዳን ፡ ጠንቅቀን ፡ አውቀናል እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብለናል ለተቸገረው ፡ ሰው ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ሲጠሩህ ፡ የምትሰማ ፡ በእሳት ፡ የምትመልስ የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ዛሬስ ፡ መች ፡ ደክመሃል በስምህ ፡ ተወራርደን ፡ ስንቱን ፡ ድል ፡ አድርገናል አዝ:- ለአምላክነትህ ፡ በነፍስ ፡ ተወራርደን ሁሉንም ፡ ጣልንና ፡ አንተን ፡ ተከተልን (፪x) በዘመናት ፡ መሃል ፡ በድል ፡ ተሻግረናል ልንክደው ፡ አንችልም ፡ ክንድህን ፡ አይተናል ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x) ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x) በችርነትህ ፡ አመታትን ፡ ለህዝብህ ፡ ታቀናጃለህ ምድረ ፡ በዳው ፡ ስብ ፡ ይጠግባል ፡ ባሕሩን ፡ ታሻግራለህ ከጠላት ፡ ዛቻ ፡ በሚገርም ፡ ታምራትህ ፡ ካመለጥን በነፍሳችን ፡ ተወራርደን ፡ ይገባል ፡ አንተን ፡ ልናምን አዝ:- ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ያየታሪክ ፡ መዝገብ ያደረከው ፡ በይፋ ፡ ይነበብ እውነት ፡ ነው ፡ ዘመን ፡ ይናገራል እግዚአብሔር ፡ ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ የታል (፪x) ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x) ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x) ሁሉን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥለን ፡ ተከተልንህ እንደወደድክ ፡ አርገህ ፡ ይሄው ፡ ምራን ፡ አልንህ ምች ፡ ከሰርን ፡ ታዲያ ፡ በብዙ ፡ አትርፈናል በአንተ ፡ እንዳማረብን ፡ ጉዑዙ ፡ ይናገራል በሚታየው ፡ ነገር ፡ ሕይወትን ፡ ሳንተምን በእምነት ፡ ከቃልህ ፡ ጋር ፡ መራመድ ፡ መረጥን ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ ስምህ ፡ አድኖናል ስትደግፈን ፡ ያዩ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ብለዋል አዝ:- ለአምላክነትህ ፡ በነፍስ ፡ ተወራርደን ሁሉንም ፡ ጣልንና ፡ አንተን ፡ ተከተልን (፪x) በዘመናት ፡ መሃል ፡ በድል ፡ ተሻግረናል ልንክደው ፡ አንችልም ፡ ክንድህን ፡ አይተናል ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x) ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.