Loading
ለአንዱ ፡ ሲነጋለት ፡ ለአንዱ ፡ ሲመሽበት በጠራራው ፡ ፀሐይ ፡ ቀን ፡ ሲጨልምበት የሰው ፡ ማንነቱ ፡ በገንዘብ ፡ ሲለካ ሃያል ፡ በጉልበቱ ፡ በኃይሉ ፡ ሲመካ በገንዘብ ፡ ታፍናለት ፡ ስትደበቅ የታመነ ፡ ወድቆ ፡ የቀጠፈ ፡ ሲደርቅ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጉዳይ ፡ ፍርድ ፡ ጐዶሎ ፡ ነው በዘመኔ ፡ ታዘብኩ ፡ በዐይኖቼ ፡ ይህን ፡ አየሁ አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው ለመበለቷ ፡ በቅን ፡ ይፈርዳል የሃዘንተኛውን ፡ እንባ ፡ ያብሳል ለተገፋው ፡ ሰው ፡ ለምስኪን ፡ አዛኝ የተሰበረውን ፡ በቃል ፡ ጠጋኝ ይኼ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የተመማነኩበት ይኼ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት (፪x) ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ ፡ ልብ ፡ ያለው ፡ ይመከር እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር (፪x) እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው ያጣ ፡ እያገኘ ፡ ያገኘም ፡ እያጣ የወጣም ፡ ወረደ ፡ የወረደም ፡ ወጣ እንደጊዜው ፡ ሆኖ ፡ ሕይወት ፡ ሲቀያየር ሃያል ፡ ጉልበት ፡ አጥሮት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲበቀል በሚያልፈው ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ እንዴት ፡ ተስፋ ፡ ይጣላል ሸመቆ ፡ አይደል ፡ አንድቀን ፡ ይከዳል የልብ ፡ ጓደኛህ ፡ እስከሞት ፡ የሚወድ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ አዝ፦ ፍርዱ ፡ የማይጓደል ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ ቃሉን ፡ ያማያጥፍ ፡ ታማኝ ፡ ጓደኛ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስን ፡ ብቻ ልብ ፡ ያለው ፡ ልብ ፡ ይበል ፡ እውነት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው ይኼ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የተመማነኩበት ይኼ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልቤን ፡ የጣልኩበት (፪x) ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ ፡ ልብ ፡ ያለው ፡ ይመከር እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር (፪x) እርሱ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ነው እርሱ ፡ ነው ፡ መንገድ ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.