Loading
አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x) አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x) በቀስተ ፡ ዳመና ፡ ከሰማይ ፡ ይመጣል ተሞሽረሽ ፡ ቆይው ፡ አክብሮ ፡ ይወስድሻል የሰርጉ ፡ ቀን ፡ ቀርቧል ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ እንዳለሽ: ሁኚለት: ተይ: ገሸሽ: አትበይ ውዴ ፡ ውዴ ፡ እያለ ፡ በናፍቆት ፡ እየጠራ ወደ ፡ አንች ፡ ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ በዳመና (፪x) አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x) የሰርግሽን ፡ ዕለት ፡ ዘንግተሽ ፡ ከሆነ ዛሬ ፡ ተዘጋጂ ፡ ዘመኑ ፡ ቀረበ ምልክቶች ፡ ሞልተው ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠበቃል አይዘገይም ፡ ደግሞ ፡ በፍጥነት ፡ ይመጣል ማራናታ ፡ እያልሽ ፡ ያለቀሽው ፡ እንባ ይታበሳል ፡ ፈጥኖ ፡ ልብሽ ፡ ብቻ ፡ ይጥና (፪x) አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x) አንቺን ፡ ፈልገውሽ ፡ በዙሪያሽ ፡ ሚያደቡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ ለመዋጥ ፡ የጓጉ ድንግልናሽን ፡ ግን ፡ አጥብቀሽ ፡ ጠብቂ ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ ቁሚ ፡ ተጠንቀቂ የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ እውነተኛው፡ መሲህ ሊመጣ ፡ ነውና ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ (፪x) አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.