Loading
ጊዜው ፡ እየከፋ ፡ ሲሄድ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ያደርጋል ጥፋት ፡ ሲበዛ ፡ ወዴት ፡ ይሸሻል መተማመን ፡ ጠፍቶ ፡ ጥላቻ ፡ ሲበረታ የተለፋበት ፡ ሁሉ ፡ ድርምስምስ ፡ ሲል ቀና ፡ ነው ፡ የተባለው ፡ ቅጡ ፡ ሲጠፋ ሰው ፡ ግራ ፡ ተጋብቶ ፡ ጭንግር???ጭምር??? ፡ ሲለው ወደማን ፡ ነው ፡ የሚያየው አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ እንጸልይ ፡ ሳንታክት እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x) በድህነት ፡ ቀመር ፡ ተጠፍሮ ህዝብ ፡ በድካም ፡ ጅራፍ ፡ ሲገረፍ ሞትን ፡ እንደጨለማ ፡ ምድራችንን ፡ ሲከብ አንዱ ፡ ከአንዱ ፡ ሲጋደል አለቆች ፡ አልፈቱም ፡ ይህን ፡ እንቆቅልሽ ከአዋቂቆችም ፡ ምክር ፡ አልተገኘም ነገሥታት ፡ እነርሱ ፡ ተሰወረባቸው ድንግዝግዝ ፡ አለ ፡ ቀኑ አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ እንጸልይ ፡ ሳንታክት እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x) እንጸልይ በስሜ ፡ የተጠሩ ፡ ህዝቤ ራሳቸውን ፡ አዋርደው ፡ ቢጸልዩ ከሰማይ ፡ ሆኜ ፡ እሰማለሁ ምድራቸውን ፡ እፈውሳለሁ ብሏል ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ እንጸልይ ፡ ጸሎት ፡ የሚሰማ ፡ አምላክ ፡ አለ እንጸልይ ፡ ሳንታክት እንጸልይ ፡ ፍርድን ፡ የሚወድድ አምላክ ፡ አለ ፡ በሰማይ (፪x) እንጸልይ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.