Loading
የሹዋ ፡ ሮሓሚን ኤል ፡ ሮሓሚን አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ ላያስበው ፡ መልሶ እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x) አላውቀውም ፡ ቢል ፡ ቢምል ፡ ቢክድም ራሱን ፡ ሊያድን ፡ ራሱን ፡ ቢወድም መልሶ ፡ ሲያዝን ፡ ሲፀፀት ፡ አየው የመንግሥቱን ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ አስጨበጠው ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x) አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ ላያስበው ፡ መልሶ እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x) ኃጢአት ፡ ቢያደርግም ፡ ምልስ ፡ ልብ ፡ ይዟል የምህረቱን ፡ ደጅ ፡ ፈጥኖ ፡ ያንኳኳል የተጻፈልን ፡ ለትምህርት ፡ ነው ምስክሩ ፡ ግን ፡ እንደ ፡ ልቤ ፡ ነው ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x) አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ ላያስበው ፡ መልሶ እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x) ድርሻውን ፡ ወስዶ ፡ ትቶ ፡ ቢወጣ እንዲያው ፡ ሲባዝን ፡ መቅኖውን ፡ አጣ ባሪያ ፡ ልሁን ፡ ሲል ፡ ዕድል ፡ ካገኘሁ የጠበቀው ፡ ግን ፡ ልጅነቱ ፡ ነው ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x) አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ ላያስበው ፡ መልሶ እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x) አዶናይ ፡ ሮሆሚን ራፋዬል ፡ ሮሆሚን መሲያሕ ፡ ሮሆሚን ኤል ፡ ሮሆሚን አዶናይ ፡ ሮሆሚን የሱዋ ፡ ሮሆሚን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.