Loading
አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x) ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x) ለምን ፡ እፈራለሁ ፡ እንዴትስ ፡ እሰጋለሁ (፪x) የዘለዓለም ፡ ኪዳን ፡ ከአንተ ፡ ተቀብያለሁ (፪x) ዘመናቴን ፡ ቆጥረህ ፡ አውቀሃል ፡ እርምጃዬን (፪x) ትላንትም ፡ አይቆጨኝ ፡ ነገም ፡ አያስፈራኝ (፬x) አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x) ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x) በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ በነፍሴ ፡ የተጻፈው (፪x) በዓመታቶቼ ፡ ላይ ፡ ክብርህ ፡ የተገለጠው (፪x) ድንቅ ፡ ተዓምራትህ ፡ ቃላትም ፡ የማይገልጸው (፪x) መኖሬ ፡ እራሱ ፡ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነው (፬x) አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x) ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x) ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ እየተከታተሉኝ (፪x) የሥምህ ፡ ጉልበቱ ፡ ከሞት ፡ ስላስጣለኝ (፪x) በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥምህን ፡ እጠራለሁ (፪x) በሕያዋን ፡ አገር ፡ በፊትህ ፡ እኖራለሁ (፪x) ቤትህ ፡ እኖራለሁ (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x) ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.