Loading
የሰላም ፡ አለቃ ፡ የዘለዓለም ፡ አባት ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ፡ የተገባው ፡ ስግደት ድንቅ ፡ መካር ፡ አምላክ ፡ ሃያልም ፡ ይባላል ስልጣን ፡ አለቅነት ፡ ለእርሱ ፡ ተሰጥቶታል አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x) መንገድና ፡ ሕይወት ፡ እውነትም ፡ ነኝ ፡ ያለው በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ብርታትና ፡ ጥበብ ፡ ኃይልም ፡ የተሞላው ክብሩ ፡ የገነነ ፡ ምሥጋናው ፡ ብዙ ፡ ነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x) የክንፉ ፡ መዘርጋት ፡ ምድርን ፡ ይሸፍናል በሰማይ ፡ ሰማያት ፡ በክብር ፡ ይራመዳል የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው በትንሳኤ ፡ በኩል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x) ሲዘባበቱበት ፡ አፉን ፡ አልከፈተም በከሳሾቹ ፡ ፊት ፡ ቆሞ ፡ አልተሟገተም ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ . (1) . ፡ ያስቀራል ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ጉልበትም ፡ ይገዛል አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x) ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ወገኑን ፡ ለይቷል የሕይወትን ፡ መዝገብ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈቷል ነፍሱን ፡ ቤዛ ፡ ሰጥቶ ፡ ብዙዎችን ፡ ማርኳል ከሃያላንም ፡ ጋር ፡ ምርኮን ፡ ይካፈላል አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፪x) ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ የሚያገለግሉት ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ የሚሉት ያለ ፡ የነበርነው ፡ ደግሞም ፡ ይመለሳል ለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ መንግሱ ፡ ይጸናል አዝ፦ ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የወደደኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ የማመልከው ፡ ማነው የመረጠኝ ፡ ማነው ፡ ይህ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው ለዘለዓለም ፡ አምካኬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ጌታዬ ፡ ነው ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ንጉሤ ፡ ነው (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.