Loading
አምላክነትህን ፡ ታላቅነትህ ፡ ጌትነትህ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x) አምላኬ (፫x) ፡ እያልኩኝ በፊትህ ፡ ብሰግድ ፡ ያለኝን ፡ ባስቀምጥ ቃላት ፡ አላገኝም ፡ ክብርህን ፡ የሚገልጥ (፪x) አዝ፦ መልካምነትህ ፡ አባትነትህ ፡ ደግነትህ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x) ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ ተከትለውኛል በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ ፍቅርህ ፡ ደግፎኛል መልካም ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ በስጦታህ ፡ አትጸጸት ቆጥሬ ፡ አልጨርስም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ደግነት (፪x) አዝ፦ መልካምነትህ ፡ አባትነትህ ፡ ደግነትህ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x) በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ የማውቀው ፡ እውነቱ ቀዝቅዞ ፡ አያውቅም ፡ መውደድህ ፡ ግለቱ የፍቅርህ ፡ ስፋቱ ፡ ልክ ፡ የለው ፡ ጥልቀቱ በመስቀል ፡ ተገልጧል ፡ አምሳያ ፡ ማጣቱ አዝ፦ አምላክነትህ ፡ ታማኝነትህ ፡ ወዳጅነትህ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.