Loading
እንዲህ ፡ አልነበረም ፡ ታሪኬ አንተ ፡ ሳትገባ ፡ በሕይወቴ (፪x) ውስጤን ፡ ስትነካው ፡ ታወቀ ፡ በፊቴ አሳርፈኸኛል ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ (፪x) አንተ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ አመሰግናለሁ ፡ ተመስገን ፡ አባቴ (፪x) ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል ዘለዓለም ፡ በቤትህ ፡ ያኖሩኛል (፪x) እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው ፡ የሚያሳጣኝ ፡ አንድም ፡ ነገር ፡ የለም በለመለመው ፡ መስክ ፡ ይመራኛል ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ያሳድረኛል ነፍሴን ፡ መለሳት ፡ ስለስሙ ፡ በጽድቅ ፡ መንገድ ፡ መራኝ በሞት ፡ መሃከል ፡ እንኳን ፡ ብሄድ እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነውና ፡ ክፉን ፡ አልፈራም ፡ እኔ ፡ አልፈራም ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ የሆነው ይህ ፡ ነው ፡ አይባልም ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ ነፃ ፡ እንድሆን ፡ ሁሉን ፡ ሆኖልኛል ሞቴንም ፡ በሞቱ ፡ ጌታዬ ፡ ለውጧል (፪x) አንተ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ አመሰግናለሁ ፡ ተመስገን ፡ አባቴ (፪x) ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል ዘለዓለም ፡ በቤትህ ፡ ያኖሩኛል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.