Loading
ሰማይን ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ምድርን ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ ነው ታዲያ ፡ እኔ ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ ታዲያ ፡ እኔ ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ፡ በደስታ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ እርሱ ፡ ተናግሯል ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል ጌታ ፡ ተናግሯል ፡ ቤተሰቤ ፡ ላይ የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል ጌታ ፡ ተናግሯል ፡ በሃገሬ ፡ ላይ የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል እግዚአብሔር ፡ በማን ፡ ይመሰላል ፡ ከማን ፡ ጋራ ፡ ይወዳደራል የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነው ፡ ኃይሉ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው ጐበዝ ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ ይወድቃሉ ፡ ኃይለኞች ፡ ደግሞ ፡ ይደክማሉ ጌታን ፡ መመኪያ ፡ ያደረጉ ፡ ሕይወታቸውን ፡ ለርሱ ፡ የሰጡ ይወጣሉ ፡ ይሮጣሉ ፣ ከቶ ፡ አይደክሙም ፡ ያሸንፋሉ ከፍታውን ፡ ይይዛሉ እወጣለሁ ፡ ገና ፣ እሮጣለሁ ፡ ከቶ ፡ አልደክምም ፡ አሸንፋለሁ ከፍታውን ፡ እይዛለሁ እይታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ የእኔስ ፡ ኑሮ ፡ ሰማያዊ ፡ ነው አምኖ ፡ በምድር ፡ አሰማርቶኛል ፡ ማንነቴን ፡ ተርክ ፡ ብሎኛል ለተጠማ ፡ እርካታ ፡ ለደከመው ፡ ጉልበት ፡ ላዘነው ፡ ደስታ ይህን ፡ እንደሚሰጥ ፡ ነው ፡ ማውቀው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) ይሄ ፡ ነው ፡ የተጻፈው ይሄ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የተባለልኝ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.