Loading
የትላንቱን ፡ ነገር ፡ ጌታዬ ፡ ካስረሳኝ አምናን ፡ አሳልፎ ፡ ለዛሬ ፡ ካበቃኝ ስለነገው ፡ ደግሞ ፡ አምኜ ፡ ልናገር አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከቶ ፡ የማይደክመው ፡ ስለእኔ ፡ ሚናገር (፫x) አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከቶ ፡ የማይደክመው ፡ ስለእኔ ፡ ሚናገር (፪x) አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ አለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አለ አለ ፡ የሚመራኝ ፡ አለ አለ ፡ የሚራራልኝ ፡ አለ አለ ፡ አለ (፪x) እረኛ ፡ እንደሌለው ፡ አልቅበዘበዝም በሚነፍሰው ፡ ንፋስ ፡ አልነዋወጥም መሠረቴ ፡ ጽኑ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተናገረውን/የተናገረኝ ፡ ሲያደርግ ፡ አይቻለሁ (፪x) የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተናገረኝ ፡ ሲያደርግ ፡ አይቻለሁ (፪x) አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ አለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አለ አለ ፡ የሚመራኝ ፡ አለ አለ ፡ የሚራራልኝ ፡ አለ አለ ፡ አለ (፪x) እንዳለኝ ፡ እኖራለሁ ፡ እንደተናገረኝ የምትረግጠው ፡ ምድር ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ እንዳለኝ (፪x) እንደንስር ፡ በሰማይ ፡ በከፍታ ፡ እበራለሁ እንደአንበሳ ፡ ደቦል ፡ በምድር ፡ እመላለሳለሁ እመላለሳለሁ (፫x) ፡ ከልካዬ ፡ ኧረ ፡ ማነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.