Loading
የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x) አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x) የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x) አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x) አሃሃሃ ፡ ጠላቴ ፡ ሊያመልጥ ፡ ለምን ፡ ይሞክራል የእግዚአብሔር ፡ እሳት ፡ ዙሪያውን ፡ ከቦታል ኤልያስ ፡ የእስራኤል ፡ ነው ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ሆኗል እግዚአብሔር ፡ ቅባቱን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ለቆታል የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው(፪x) ለታሰሩት ፡ መፈታት ፡ ላዘኑት ፡ መጽናናት ፡ እናገር ፡ ዘንድ ፡ ልኮኛል ጌታ ፡ መንፈሱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ የቀባኝ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረኝ ጐልያድን ፡ እንድመታ ፡ ያንን ፡ ያዝጋጀኝ ልባቹህ ፡ አይውደቅ ፡ በጩኸቱ ፡ ብርታት ተመቶ ፡ ይወድቃል ፡ በአምላኬ ፡ ጉልበት የጨለማ ፡ ስልጣን ፡ ጥቃት ፡ በዝቶበታል የእኔ ፡ ነው ፡ ያለውን ፡ ለቆ ፡ ሲሸሽ ፡ ታይቷል ፓውሎስ ፡ ጴጥሮስ ፡ የሉም ፡ እኛን ፡ ተክተዋል ለእኔ ፡ ለአንተ ፡ ለአንቺ ፡ አደራ ፡ ሰጥተዋል የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x) አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x) የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x) አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.